የክፍለ ከተማው እና ወረዳው አስተባባሪ ኮሚቴዎች መልእክት

ብልጽግና ፓርቲ ሀገር በቀል፣ ገቢር ነበብ ፣ አካታች፣ ተደራሽ  አና በኢትዮጵያ  ተጨባጭ አቅሞች ላይ በተመሠረተ  የፖለቲካ  እሳቤ የሚመራ  ፓርቲ ነዉ። ብልፅግና የኢትዮጵያን አቅሞች በመደመር እሳቤ በማሰባሰብ ፣ ጥንካሬዎችን በማስቀጠል፣ ሰህተቶችን  በማረም፣ የተዛቡ ትርክቶችን በማረቅ  በጋራ የመልማትን፣ በትብብር  የማደግን አቅጣጫ  ይከተላል። ይህ አዲስ ፖለቲካዊ እይታ ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ደረጃ  ማሸጋገሪያ ሀዲድ ፤ የተጀመረዉን ለዉጥ ለማፅናትም  አቅም ነዉ።

ወ/ሮ ካባ መቡራቴ

የን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ

ብልፅግና ፓርቲ ቃሉን በተግባር በመፈጸም  አዲስ አበባን  ስሟንና ታሪኳን በሚያድስና የአፍሪካ መዲናነቷን በሚመጥን ሁኔታ ከብክለት የፀዳች ፅዱ፣ ውብና ለነዋሪዎቿ ተስማሚ ለማድረግ ዘርፈ- ብዙ ተግባራትን አከናውኗል። አዲስ አበባን የሁለንተናዊ ብልጽግና ተምሳሌትነቷን ለማረጋገጥ በኘላን የምትመራና የተሟላ የከተማ ስርዓት ያላት  ለማድረግ ፓርቲያችን የያዝነውን ራዕይ እዉን ይሆን ዘንድ ባላሰለሰ ጥረት በርካታ ተስፋ ሰጭና ተጨባጭ የሆኑ ዉጤቶችን ማስመዝገብ ተችሏል፡፡ በዚህም የፓርቲያችንን ዕሴት በጠበቀ መልኩ በከተማዋ  መጭውን ትውልድ ታሳቢ ያደረጉ አዳጊና ዘመን ተሻጋሪ የሆኑ በርካታ ማህበራዊና ኢኖሚያዊ ዕምርታዎች ተመዝግበዋል

አቶ መብራቱ ደሴ

የን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ

አንድነታችንን በማጠናከር የብልፅግና ጉዧችንን እውን እናደርጋለን !! ብልፅግና ፓርቲ የኢትዮጵያን ብልጽግና በሁሉ አቀፍ ማዕቀፍ ማረጋጋጥ የሚል ትልቅ ማሰብን መሠረት አድርጎ እየተንቀሳቀሰ ያለ ፓርቲ ነው። ለታላቋ ኢትዮጵያ ትልቅ ማሰብ የኢትዮጵያን ሁሉ አቀፍ ፀጋዎችን ከመረዳት እና ስብራቶቿን ለማከም ቁርጠኛ ከመሆን ባሻገር ብልፅግናን እንደ ራዕይና ግብ መያዝ ትልቅ ከማሰብ፣ ብርታትንና ፅናትን አቅም አድርጎ ፈተናዎችን ተቋቁሞ ለመሻገርም ከመወሰን የሚመነጭ ነዉ። መዳረሻው ብልፅግና መሆኑን ግልፅ ያደረገው ፓርቲያችን ጉዞዎቹ ሁሉ ነገን ታሳቢ ያደረጉ በመሆናቸው ለዘላቂ ልማት፣ ለዘላቂ ሰላም በህብረ - ብሔራዊ አንድነት አሻራዎቻችንን  ማሳረፉን አጠናክረን እንቀጥላለን

አቶ ጉዲሳ ገቢሳ

የን/ስ/ላ/ክ/ከተማ የኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን ቅ/ፅ/ቤት ኃለፊ

መዳረሻው ብልፅግና መሆኑን ግልፅ ያደረገው ፓርቲያችን ጉዞዎቹ ሁሉ ነገን ታሳቢ ያደረጉ በመሆናቸው ለዘላቂ ልማት፣ ለዘላቂ ሰላም በህብረ - ብሔራዊ አንድነት አሻራዎቻችንን  ማሳረፉን አጠናክረን እንቀጥላለን

አቶ ዘሪሁን አሰፋ

የወረዳ 14 ዋና ስራ አስፈፃሚ

ብዝሀነት አቅም ነው፤ ብዝሀነት ፀጋ ነው፤ ብዝሀነት የሀገራችን ተጨባጭ እውነታ ነው፡፡ በመሆኑም ብዝሀ መልካችን የሚንፀባረቅበት ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ስርዓት ለመገንባት ብልፅግና እንደ ፓርቲ በፅናት ይታገላል፡፡ አንዱን ጥሎ አንዱን አንጠልጥሎ ሀገር ስለማይገነባ የሀሳብ ብዝሀነትንም ጭምር ለማስተናገድ በግራና በቀኝ የተወጠሩ የፅንፍ አስተሳሰቦችም ወደ መሀል ተቀራርበው ሀገር የማፍረስ ሳይሆን ሀገር የመገንባት ሚና እንዲኖራቸውም ፓርቲያችን በአርአያነት ይንቀሳቀሳል፡፡

አቶ ጥላሁን ሽታ

የወረዳ 14 ም/ስራ አስፈፃሚ እና የስራና ክህሎት ፅ/ቤት ኃላፊ

ፓርቲያችን ብልጽግና  ቃል በገባው መሰረት አዲስ አበባን ጽዱና ውብ አደርጋለው ባለው መሰረት  አዲስ አበባ የብልጽግና ተምሳሌትነቷን እያፀናች ያለች ከተማ ሆናለች የብዙሃን መዲና የሆነችው  አዲስ  አበባ  የኢኮኖሚ፣  የባህል  እና  የፖለቲካ  ማዕከል ነች፤ ሆኖም  ከተማዊ ገፅታዋ  በሚመጥናት ደረጃ  ያለነበረ ጎስቋላ ሆና ቆይታለች።  በፓርቲያችን  ተደርተው የቆዩ  ስብራቶችን  በማጤን ከተማዋን ወደ ብልፅግና የሚያሻግር  ሀሳብ በመንደፍ በፍጥነትና ጥራት በመተግበር  ቃልን በተግባር ማፅናት ችሏል።

ወ/ሮ ትዕግስት ሞገስ

የወረዳ 14 ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ

ብልፅግና ከዘመኑ ጋር የሚራመድ ፣ ተለዋዋጩን ቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታ ቀድሞ የሚረዳ ፣ አሻግሮ የሚያይ ተራማጅ ፓርቲ ነው። የምንተገብራቸው ፕሮግራሞች ዛሬን ከነገ የሚያስተሳሰሩ የለውጥ ጉዟችንን ስኬት ቀጣይነትም የሚያረጋግጡ ናቸው።

አቶ አበራ ቢቂላ

የወረዳ 14 የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃለፊ

የህዝባችን የልማት፣ የእኩልነት እና የነፃነት ፍላጎቶቹ እንዲሟሉለት የሚያስችል ነፃ፣ ገለልተኛና ብቃትን መሰረት ያደረገ ሀገራዊ ተቋማዊ አደረጃጀት ለመገንባት ፓርቲያችን ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ  ይገኛል፡፡ የፓርቲ ግንባታ ጅምራችንም ጠንካራና የማይናወጥ ተቋማዊ መሰረት ያለው እንዲሆን ፓርቲያችን ግብ  አድርጎ እየተነረቀሰቀሰ ይገኛል፡፡ በተቋማዊና ህዝባዊ ባህል ላይ የሚገነባ ዴሞክራሲም ፅኑ መሰረት እንደሚኖረው ይታመናል፡፡

አቶ አሜጋ ዘበርጋ

የወረዳ 14 አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ